ማሳሰቢያ

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፈቃድ አሰጣጥ የዳግም ምዝገባ መምሪያ ቁጥር 01/2016 መሠረት ፈቃድ ወይም በቀድሞ አሰራር መሠረት የእውቅና ፈቃድ በባለስልጣኑ ተሰጥቷችሁ እየሰራችሁ የምትገኙ እንዲሁም ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት ተጠሪ ሆናችሁ ነገር ግን በፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ሳታልፉ ትምህርትና ስልጠና እየሰጣችሁ ያላችሁ ተቋማትን በአዲሱ የፈቃድ ስታንዳርድ መሠረት ግምገማ በማድረግ ለመመዝገብ የሚያስችል የዝግጅት ጊዜ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል ፡፡ በመሆኑም በተዘጋጀላችሁ እና በዚህ ሊንክ http://bit.ly/4do4ZUJ በተገለጸላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከነገ ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በባለስልጣኑ ቅጥር ግቢ በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በዳግም ምዝገባ ሂደት ውስጥ ያልገባ ተቋም መምሪያው ላይ በተቀመጠው አንቀጽ 2(11)መሠረት ከባለሥልጣኑ የወሰደው የማስተማር ፈቃድ በገዛ ፈቃዱ እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ፈቃዱ የሚነጠቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በተሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ