በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፈቃድ እና ፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ ፣ ስታንዳርዶች እና የዳግም ምዝገባ መምሪያ ላይ ውይይት ተደረገ

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የዳግም ምዝገባው ዋነኛ ዓላማዎች ተቋማት የትምህርትና እና ስልጠና መስኮቻቸውን በአዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ለመገምገም እና ለመመዝገብ፤ በፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት አልፈው ያልተመዘገቡ ተቋማትን በመገምገም እንደ ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ፤ ባለስልጣኑ የተሟላና የተደራጀ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መረጃ እንዲኖረው ለማድረግ፤ በመንግስት እና በግል ተቋማት መካከል ያለውን የፈቃድ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ልዩነት ለማስቀረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው በተቀናጀ የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ አስተዳደር ስርዓት(HEMIS ) ያስገቡ ተቋማት ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘም 87 በመቶ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውደቃቸውን ፤ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን፤የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ ብቻ መሆኑን እና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት በወ/ሮ ሂወት አሰፋ በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፈቃድ እና ፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ ፣ ስታንዳርዶች እና የዳግም ምዝገባ መምሪያ ዙሪያ ገለጻ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በትምህርት ሚኒስቴር በፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ እና በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ