በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት የእውቅና ውሳኔ እና የቆይታ ጊዜ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት የእውቅና ውሳኔ እና የቆይታ ጊዜ -------------------------------------------------------------------------------------------------- ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና የሚሰጥ ውሳኔ በግምገማው ውጤት መሠረት :- ** ሙሉ እውቅና በተደረገው የእውቅና ግምገማ ተቋሙ ወይም ፕሮግራሙ ያገኘው ውጤት በባለስልጣኑ በወጣው የውጤት መወሰኛ መምሪያ መሠረት ከፍተኛ ውጤት ክልል ውስጥ ሲገኝ ለአምስት ዓመት የሚሰጥ ይሆናል። ** በሁኔታ የተገደበ እውቅና በተደረገው የእውቅና ግምገማ ተቋሙ ወይም ፕሮግራሙ ያገኘው ውጤት በባለስልጣኑ በወጣው የውጤት መወሰኛ መምሪያ መሠረት መካከለኛ ውጤት ክልል ውስጥ ሲገኝ ለሶስት ዓመት የሚሰጥ ይሆናል። ** የእውቅና ክልከላ 1. በተደረገው የእውቅና ግምገማ ተቋሙ ወይም ፕሮግራሙ ያገኘው ውጤት በባለስልጣኑ በወጣው የውጤት መወሰኛ መምሪያ መሠረት በተቀመጠው ዝቅተኛ የውጤት ክልል ውስጥ ሲገኝ የሚከለከል ይሆናል። 2. የተቋም ወይም የፕሮግራም እውቅና የተከለከለ ተቋም ዳግም የእውቅና ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው ክልከላው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከአንድ ዓመት በኋላ ይሆናል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።