የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ

ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በኢፌዲሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ክብር ነጻነት እና ሉዓላዊነት በሚል የተዘጋጀ ለውይይት መነሻየሚሆን ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፣ የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ እና የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ የውይይት ሰነድ መሠረት በማድረግ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፣ የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ እና የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ክብር ነጻነት እና ሉዓላዊነት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ