የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የፌደራል መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ

የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የፌደራል መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ ================ ============== ======== ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በኢፌዲሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የፌደራል መንግስት የ2016 የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች አቅርበዋል፡፡ ኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ እና የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ የቀረበውን የውይይት ሰነድ መሠረት በማድረግ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ እና የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ