የ2016 ዓ.ም የጳጉሜን አምስት ቀናት ስያሜዎች እና ቀለማት
የ2016 ዓ.ም ጳጉሜን አምስት ቀናት በተለያየ መርሃ-ግብር ለማክበር ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡ የ2016 ዓ.ም. የጳጉሜን አምስት ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች በመስጠት በነዚህ ቀናት የሚካሄዱ መርሃ-ግብሮች ቀኑን ከማክበር ባለፈ ተቋማዊ አገልግሎቶቻችንን እና ሀገራዊ ተልዕኳችንን ካለፉት ዓመታት በተሻለ ደረጃ በማሻሻል ስራችንን በአግባቡ የምንፈጽምበት እንዲሆን ያግዘናል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታትም እንዲሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የጳግሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች በመስጠት ሲከበር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ዓመትም፡- ጳጉሜን1፡-የመሻገር ቀን ጳጉሜን 2፡- የሪፎርም ቀን (ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት) ጳጉሜን 3፡- የሉዓላዊነት ቀን ጳጉሜን 4፡- የህብር ቀን ጳጉሜን 5፡- የነገ ቀን በሚል አምስቱንም የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ መርሃ- ግብሮች ይከበራሉ:: የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በተሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ