የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያዩ

ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የባለሥልጣኑ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የስራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ እንዳሉት የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ስራን ዲጂታላይዜሽን መደረጉ ፤መልካም አስተዳደር እና ግልጸኝነትን ለማረጋገጥ 5 መመሪያዎች እና 13 ስታንዳርዶች ጸድቀው ስራ ላይ መዋላቸው፤በባለሥልጣኑ የሚሰጡት አገልግሎቶችን በማዘመን ቀልጣፋ እና ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ማከናወን መቻሉ ፤የፈቃድና ፈቃድ እድሳት ስራዎች ፤የክትትል ስራዎች እና ለእውቅና አሰጣጥ ስራ መነሻ የሚሆኑ የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት መቻሉ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በባለሥልጣኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት አመለወርቅ ደሳለኝ በበኩላቸው በ2017 በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚሰሩ ሥራቸው መካከል የፈቃድ፣ የእውቅና አሰጣጥ፣ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እና ጥራት ኦዲት ጥያቄዎች መልስ መስጠት፤ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ማካሄድ ፤የባለስልጣኑን የኢንፎርሜሽን እና ኮሚዩኔኬሽን ማጠናከር ፤ አገልግሎቶችን ማዘመን ፤ የሰው ሀይል ማሟላት ፤ የሠራተኞች አቅም ግንባታ እና ለአዲሱ የህንጻ ግንባታ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲጠናቀቅ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ