16ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በባለሥልጣኑ ተከበረ
የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ ቃል 16ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም በባለሥልጣኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ ፡፡ በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን በማንሳት ፣ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ መልእክቶችን በማስተላለፍ፣ በሉዓላዊነት መገለጫና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ምልክት በሆነው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ-መሀላ በመፈጸም እና ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር በዓሉ ተከብሮ ውሏል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ
