ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች የዲጅታል የሀብት ምዝገባ አተገባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
-------------------------------------------------------------------------------------------
ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የዲጅታል የሀብት ምዝገባ አተገባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ታምሩ መስፍን በስልጠናው መክፈቻ ላይ በአስተላለፉት መልእክት እንዳሉት የዲጅታል ሀብት ምዝገባ አተገባበርን አስመልክቶ እንደ ሀገር የተቀመጠውን አቅጣጫ ከመተግበርና ከማስተግበር አንጻር ሁላችንም የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ተሳተፊ በመሆናችን የሚጠበቅብንን ሁሉ መሠረታዊ መርሆዎችን ከግምት በማስገባት ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በባለሥልጣኑ የስነምግባርና መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መቅደስ ወንዱአንተ በበኩላቸው ስለስነምግባርና መከታተያ ክፍል መቋቋም፤ ስለስነምግባር መከታተያ ክፍሉ ዓላማ፤ የስነምግባር መከታተያ ክፍሉ ስለሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የዲጅታል የሀብት ምዝገባ አተገባበርን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የቀረበውን የስልጠና ሰነድ መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ የስነምግባርና መከታተያ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ወንዱአንተ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።
Newsroom
ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች የዲጅታል የሀብት ምዝገባ አተገባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ETA
Education & Training Authority
December 31, 2025
1 min read