Skip to content
Newsroom

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መስፈተርቶች/ስታንዳርዶች/መሠረት የስርዓተ ትምህርት መስፈርቶች

ETA Education & Training Authority November 03, 2026 1 min read
የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መስፈተርቶች/ስታንዳርዶች/መሠረት የስርዓተ ትምህርት መስፈርቶች

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መስፈተርቶች/ስታንዳርዶች/መሠረት የስርዓተ ትምህርት መስፈርቶች

አንድ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ለሚያካሂደው ስልጠና ፕሮግራም በአግባቡ የተቀረፀ ስርዓተ ትምህርት ሊኖረው ይገባል።
✔️የኢትዮጵያ የሙያ ደረጃን መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት፤
✔️ፕሮግራሙ ከገበያው ፍላጎት ጋር የተገናዘበ ሰልጣኙን ለስራ የሚያዘጋጅ ብቁ ዜጋ የሚያፈራና አግባብነት ያለው መሆን ይኖርበታል ፤
✔️እያንዳንዱ ሞጁል የተሟላ የሞጁል ዓላማ፣ የሞጁል ዲስክሪብሽን፣ የማሰልጠኛ ዘዴዎች፣ የምዘና ዘዴዎች፣ የማሰልጠኛ እና ማጣቀሻ መፅሐፍት በግልጽና በዝርዝር የተዘጋጀለት መሆን አለበት ፤
✔️በሀገር ውስጥ ከዚህ ቀደም ተሰጥቶ የማይታወቅ ፕሮግራም ከሆነ የገበያ ፍላጎት ያለው ለመሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል የሙያ ደረጃም ሊዘጋጅለት ይገባል፤
✔️አግባብነት ያላቸው የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች (መፃህፍት፣ የኢንተርኔት አቅርቦት፣ ቪዲዮ ቴፖች፣ ወዘተ…)፤
✔️የኢትዮጵያ የሙያ ደረጃ ባስቀመጠው መሠረት አግባብነት ያላቸው የስልጠና ቁሳቁሶች፣ ማቴሪያል እና ሌሎች ግብአቶች፤
✔️ባለሥልጣኑ ባወጣው መመሪያ (guide line for the inclusion of people with disabilities in TVT) መሠረት ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ፍላጎቶች ተጣጣሚ ሆኖ መዘጋጀት ይኖርበታል።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ ።

News Announcement
Share