የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2024 አቻ ግመታን በተመለከተ:-

የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2024 አቻ ግመታን በተመለከተ:- --------------------------------------------------------------------------------------------------- ** ለምዘና ከቀረበው የትምህርትና ስልጠና ማስረጃ ጋር የተያያዙ የሙያ መጠሪያ ስያሜ የማዕረግ ስያሜ እና የሙያ ፍቃድ ሲኖር ምዘናው የሚከናወነው ለትምህርት እና ስልጠናው ማስረጃ ወይም ደረጃው ብቻ ነው፡፡ ** ባለስልጣን መስሪያቤቱ የምዘና አገልግሎት የሚሰጠው ለትምህርት እና ስልጠና ማስረጃ ብቻ ሲሆን ከውጭ ሀገር የተሰጠ የአቻ ግምት ማስረጃ ወይም የሙያ ፍቃድ ወይም ሌላ ከትምህርት ወይም ስልጠና ማስረጃ ውጭ ያለ ማንኛውም ማስረጃ የምዘና አገልግሎት አይሰጠውም፡፡ ** የቀረበው የትምህርት ወይም ስልጠና ማስረጃ ጊዜያዊ ከሆነ ኦሪጂናሉ እስከሚቀርብ ድረስ ለ6 ወራት የሚያገለግል ጊዜአዊ የምዘና ምስክር ወረቀት ይሰጠዋል፡፡ ጊዜአዊ የምስክር ወረቀቱ ለ2ኛ ጊዜ ለ 6 ወራት ብቻ የሚያገለግል ዕድሳት ሊሰጠው ይችላል፤ ለ3ኛ ጊዜ ግን ዕድሳትአይፈቀድም፡፡ ** ከእንግሊዘኛ ቋንቋ የተለየ ሌላ የውጭ ቋንቋ ተናጋሪ የውጭ ሀገር ዜጎች ለሙያ ፍቃድ ምዝገባ የሚያገለግል የምዘና ምስክር ወረቀት ሲፈልጉ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ** የሀይማኖት ነክ የትምህርት ማስረጃዎች የምዘና አገልግሎት አይሰጣቸውም፡፡ ** አገልግሎት ፈላጊው ያቀርበው መረጃ ከእንግሊዝኛ ውጭ በሌላ ቋንቋ የተጻፈ ከሆነ በሚመለከተው ኤምባሲ ወይም ከህጋዊ ተርጓሚ ድርጅቶች ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ** ባለጉዳዮች ከዚህ በፊት የምዘና አገልግሎት ተሰጥቷቸው ነገር ግን የምዘና ምስክር ወረቀቱ ቢጠፋባቸው ሁሉንም መስፈርት በድጋሚ አሟልተው ምትክ የምዘና ምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ ** በተሳሳተ ውሳኔ ወይም በሌላ ባልተገባ ሁኔታ የምዘና ሰርተፊኬት ለባለጉዳዮች የተሰጠ መሆኑ በበቂ ማስረጃ ሲረጋገጥ ወይም ባልተገባ ሁኔታ የተሰጠ ምስክር ወረቀት አሰራሩ አስቀድሞ ባይኖር ምስክር ወረቀቱ አያሰጥም ሊያስብል የሚችል ከሆነ ባለስልጣኑ የምዘናውን ሰርተፊኬት የመሻር ወይም ውድቅ የማድረግ ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ** የምዘና ሰርተፊኬቱ ለባለጉዳዩ የተሰጠው ከተሳሳተ ምዘና በመነጨ ውሳኔ ከሆነ ተገቢው ማሰተካከያ ተደርጎ ምትክ የምስክር ወረቀት ለባለጉዳዩ ይሰጣል፡፡ ** የተሻረው ዋናው የምዘና ሰርተፊኬት ከተሻረበት ቀን ጀምሮ ለባለጉዳዩ ወይም ለተወካዩ እንዲያውቀው ተደርጎ እና መልስ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ የተሰጠው መልስ ውሳኔውን የማያስቀይር ከሆነ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለባለስልጣኑ ተመላሽ መሆን አለበት፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።