የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/ 2016 መሠረት ስለየእውቅና አሰጣጥ ገምጋሚ ቡድን ተግባርና ኃላፊነት

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/ 2016 መሠረት ስለየእውቅና አሰጣጥ ገምጋሚ ቡድን ተግባርና ኃላፊነት -------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ** የቀረቡትን የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ሪፖርት፣ የሰልጣኝ እርካታ ዳሰሳ ሪፖርት እና የግለ- ግምገማ ሰነድን ይመረምራል፤ ** የእውቅና ግምገማ የጊዜ ሰሌዳን ያዘጋጃል፤ የመስክ ግምገማን ያካሄዳል፤ ** የመስክ ግምገማውን ሲያጠናቀቅ ለተገምጋሚው ተቋም ስለ ግምገማው ሂደት የመውጫ ሪፖርት በጽሁፍ ይሰጣል፤ ** የግምገማ ሪፖርት በማዘጋጀት ለዴስክ ኃላፊ ያቀርባል፤ እና ** ዝርዝር የገምጋሚ ቡድኑ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የቡድን አባላት አመራረጥ በባለሥልጣኑ የአሠራር ሰርዓት ይወሰናል፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።