የመረጃ አረዳድ ላይ የተፈጠረን ክፍተት ለማብራራት የተሰጠ ማሳሰቢያ
------------------------------------------------------------------
ሰኞ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ከ ኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ጋር ተያይዞ የተነሳውን ሐሳብ አስመልክቶ በስህተት በመረዳት በትላንትናው እለት “የማስተርስ ትምህርት ወደ 4 ዓመት ሊያድግ ይገባል” በሚል ርዕስ በተለያየዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር የዋለው መረጃ የአረዳድ ችግር እንጂ ምንም ዓይነት ህጋዊ መሠረት የሌለው መሆኑን እየገለጽን፤ የሁለተኛ ዲግሪ (Master Degree) ትምህርትን በተመለከተ ምንም የተቀየረ ደንብ የሌለ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
የመረጃ አረዳድ ላይ የተፈጠረን ክፍተት ለማብራራት የተሰጠ ማሳሰቢያ
ETA
Education & Training Authority
June 26, 2026
1 min read