የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/ 2016 መሠረት ስለ እውቅና አሰጣጥ አተገባበር

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/ 2016 መሠረት ስለ እውቅና አሰጣጥ አተገባበር ------------------------------------------------------------------------------------------------------- ** ባለሥልጣኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የእውቅና አሰጣጥ ሥርዓት ወጥነት እንዲኖረው ያደርጋል። ** ባለሥልጣኑ በፌደራል መንግሥት አካላት ለሚቋቋሙ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ በፌደራል ደረጃ በግል ለሚቋቋሙ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ በውጪ ዜጐች ለሚቋቋሙ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም በሌላ አገር ሕግ በተቋቋሙ ሥር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለሚተዳደሩ ማሰልጠኛ ተቋማት እውቅና ይሰጣል። ** ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በክልል የእውቅና አሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል የባለስልጣኑን የእውቅና አሰጣጥ ስርኣትና መመሪያ፣ ስታንዳርዶች እና የማስፈጸሚያ ሰነዶች መሠረት በማድረግ ፈቃድ ለተሰጣቸው ማሰልጠና ተቋማት እና ፕሮግራሞች እውቅና ይሰጣል። ** ባለሥልጣኑ በክልል ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል በባለሥልጣኑ የወጡ የአሰራር ስርአትና መመሪያ፣ ስታንዳርዶች እና የማስፈጸሚያ ሰነዶች ተግባራዊ መደረጋቸውን በሱፐርቪዥን ይከታተላል። ** ባለሥልጣኑ በክልል ህጋዊ ውክልና በተሰጠው ኣካል ተገምግመው እውቅና ባገኙ ተቋማት እና ፕሮግራሞች ላይ የናሙና ግምገማን ያካሂዳል፡፡ ** እውቅና ለመስጠት የሚደረግ ግምገማ ግልጽነት በተላበሰና አሳታፊ በሆነ ሥርዓት የሚከናወን መሆን ይኖርበታል። ** ባለሥልጣኑ በክልል የእውቅና አሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና ለተሰጠው አካል እንዲሁም ውክልና በተሰጠው አካል እውቅና ላገኙ ማሰልጠኛ ተቋማት የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ** በክልል የእውቅና አሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል እውቅና የሰጣቸውን የማስልጠኛ ተቋማት እና ፕሮግራሞች ለባለሥልጣኑ ያሳውቃል፡፡ ** ባለሥልጣኑም በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ተቋማት ዝርዝር መዝግቦ ይይዛል፤ በየአመቱም ዝርዝራቸውን ያወጣል፡፡ ** ባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ ሰነዶች ላይ ለውጦችን ወይም ማሻሻያዎችን በሚያደርግበት ጊዜ በክልል የእውቅናአሰጣጥ ስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል እንዲሁም የማሰልጠኛ ተቋማት እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።