ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኝ ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የስልጠናው ዓላማ በሀገራችን በየዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችና የሚወሰኑ ውሳኔዎች ስነምግባራዊ እንዲሆኑና የጥቅም ግጭትን ለመከላከልና ለማስተዳደር የሚያስችል አቅም ማጎልበት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህር ፣ አማካሪ እና የዩኒቨሲቲ የሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዲስዓለም በቀለ ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ትክክለኛ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊነትና ተገቢነት ያላቸው ሃሳቦችን መሠረት ያደረገ እና በሠራተኞች፤ በተቋማትና በማህበረሰብ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት አስቀድሞ በማጤንና በመተንተን ውሳኔ ለመስጠት፣ ታማኝነትና ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ምንነት፤ የዘርፎች ተጋላጭነት፣ የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር፣ የስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች፣ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የተዳሰሱ ሲሆን የጥቅም ግጭት ሙስና እንዲስፋፋ ምቹ አጋጣሚዎችን ከሚፈጥሩ መንስኤዎች አንዱ በመሆኑ ይህንን መከላከል ተገቢ መሆኑ ተገልጿ፡፡ የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህር ፣ አማካሪና የዩኒቨሲቲ የሥነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር በሆኑት ዶ/ር አዲስዓለም በቀለ እና በባለሥልጣኑ የሥነ-ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ወንዱአንተ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።