በከፍተኛ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት የክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”
በከፍተኛ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት የክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” -------------------------------------------------------------------------- #የተዘጋጁ_የአሰራር_ስርዓት_ሰነዶች ** የከፍተኛና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ ፤ ** የከፍተኛና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተማሪዎችን መረጃ አያያዝና አላላክ ማንዋል ፤እና ** 11 ቼክሊስቶች #የተከናወኑ_ተግባራት ** ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብቁ እጩ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መስፈርት ሰርኩላር ተላልፏል፤ ** በፌደራል መንግስት ወይም በውጭ ሀገር ባለሃብት ወይም በሀገር ዉስጥ በፌደራል ደረጃ ለመሰማራት የተቋቋሙ ወይም በውጭ ሀገር ህግ ተቋቁሙው ስልጠና በሚሰጡ 20 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ላይ የክትትልና ቁጥጥር ተከናውኗል፡፡ በተገኙ የስነስርዓት ጥሰቶችን ላይ ለተቋማቱ ግብረመልስ ተሰጥቷል፤ የተሰጠውንም ግብረ መልስ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲያውቀው ተደርጓል፤ ** ከባለስልጣኑ ፈቃድ ባገኙ 390 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ በሰነድ እና በአካል በተቋማቱ በመገኘት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ተከናውነዋል፤ ** በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ያልገቡና በተደጋጋሚ መስፈርቱን አሟልተው ከከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እንዲወጡ ቢጠየቁ ተግባራዊ ያላደረጉ 52 ተቋማት ላይ ህግዊ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ለሚመለከታቸው አካላት የማሳወቅ ስራ ተከናውኗል፤ ** በባለስልጣኑ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚወሰዱ የማስተካከያ የእርምት እርምጃዎችን በሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲያውቀው ተደርጓል፤እና ** የተማሪዎች መረጃ ማደራጀት፣ አያያዝ፣ አጠባበቅና አላላክ ከፍቶቶችን፤ ፈቃድ ሲስጣቸው የነበሩ ግብአቶችን ማጓደል፤ ፈቃድ ባለገኙበት ካምፓስ ማስተማር፤ፈቃድ ባለገኙበት ትምህርት መስክና መርሃ ግብር ማስተማር፤ከተፈቀደላቸው ቁጥር ተማሪዎችን መቀበል፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የማያሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር እና ማስመረቅ፤ የመውጫ ፈተና ለመፈተን ብቁ ያልሆኑ ተፍታኞችን ማቅረብ እና የተፈቀደላቸው ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ አለማድረግ በተገኘባቸው ግኝቶች እና በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ያልገቡ ተቋማት ላይ እንደየ ግኝቱ የጽሁፍ ማስጠንቀቂ፤ለተከታታይ ሁለት ዓመት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበሉ፤ ለተከታታይ 4 ዓመት በተቀጡበት የትምህርት መስክ ፈቃድ እንዳይጠይቁ፤ የትምህርት መስኩን ፣ካምፓሱን እና ተቋሙ እንዲዘጉ የማስተካክያ እርምት እርምጃ ተወስዷል፡፡ #የተሰጠ_ስልጠና_እና_የግንዛቤ_ማስጨበጫ ** ከባለስልጣኑ ፈቃድ ላገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በክትትልና ቁጥጥር መመሪያ፤ የአሰራር ስርዓቶች፤በአጋጠሙ ተግዳሮቶ እና እየተወሰዱ ባሉ የማስተካክያ እርምት እርምጃዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ 3 ጊዜ የግንዛቤ ማስጨባጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ** የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በየሲሚስተሩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብቁ እጩ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መስፈርት እና የተማሪዎችን መረጃዎች የሚያቀርቡበት አግባብ ላይ የግንዛቤ ማስጨባጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ** በፌደራል መንግስት ወይም በውጭ ሀገር ባለሃብት ወይም በሀገር ዉስጥ በፌደራል ደረጃ ለመሰማራት የተቋቋሙ ወይም በውጭ ሀገር ህግ ተቋቁሙው ስልጠና የሚሰጡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በክትትልና ቁጥጥር መመሪያና አሰራር ስርዓቶች ላይ የግንዛቤ ማስጨባጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
