“የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” በአጠቃላይ ትምህርት የኢንስፔክሽንና ቁጥጥር ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች
“የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” በአጠቃላይ ትምህርት የኢንስፔክሽንና ቁጥጥር ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች ------------------------------------------------------------------- #የተዘጋጁ_የአሰራርስርዓት_ሰነዶች ** የአጠቃላይ ትምህርት የኢንስፔክሽን ሀገራዊ ማእቀፍ መመሪያ፣መረጃ መሰብሰቢያ እና ቼክሌስት ከባለሥልጣኑ የብሔራዊ የብቃት ማእቀፍ የሥራ ክፍል ጋር በመሆን እየተሰራ ይገኛል፤ እና ** የዓለም አቀፍ ፣የማህበረሰብ እና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች የክትትልና የቁጥጥር መመሪያ በሥራ ክፍሉ ተገምግሞ እንዲጸድቅና ሥራ ላይ እንዲውል ህጋዊ አግባብነቱ እየታየ ይገኛል፡፡ #የተከናወኑ_ተግባራት ** ለመጀመሪያ ጊዜ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ በ104 ቅድመ አንደኛ ደረጃ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፤ ** በ30 የዓለምአቀፍ እና የማህበረሰብ ትምህርት ተቋማት ላይ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ተከናውኗል፤እና ** ለ9 ተቋማት በአጠቃላይ ትምህርት ቁጥጥር ወቅት በታዩ ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል፡፡ #የተሰጠ_ስልጠና_እና_የግንዛቤ_ማስጨበጫ ** ለዓለም አቀፍ እና የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ባለሀብቶች በኢንስፔክሽን አሰራር ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ** በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አሰራር ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ #የተከናወኑ_ተግባራት ** ለመጀመሪያ ጊዜ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ በ104 ቅድመ አንደኛ ደረጃ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፤ ** በ30 የዓለምአቀፍ እና የማህበረሰብ ትምህርት ተቋማት ላይ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ተከናውኗል፤እና ** ለ9 ተቋማት በአጠቃላይ ትምህርት ቁጥጥር ወቅት በታዩ ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
