በፈቃድ አሰጣጥ እና ፈቃድ እድሳት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”

በፈቃድ አሰጣጥ እና ፈቃድ እድሳት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” -------------------------------------------------------------------------- #የተዘጋጁ_የአሰራር_ስርዓት_ሰነዶች ** የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ** የፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ስታንዳርድ ** የመገምገሚያ ቼክ ሌስት እና **የዳግም ምዝገባ መምሪያ #የተከናወኑ_ተግባራት ** ፈቃድ መስጠት እና ፈቃድ ማደስ፤ ** የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ሰነድ ምርመራ እና የመስክ ምልከታ፤ ** የሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ሰነድ ምርመራ፤ ** በክልሎች እና በሁሉም ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመስክ ምልከታ፤ ** የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ሰነድ ምርመራ ሥራ መጀመር፤ ** በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የዳግም ምዝገባ የሰነድ ምርመራ እና የመስክ ምልከታ ሥራ ማጠናቀቅና ለህብረተሰቡ ይፋ ማድረግ ፤እና ** የፈቃድ አሰጣጥ ሥራን ዲጂታላይዝ ማድረግ #የተሰጠ_ስልጠና_እና_የግንዛቤ ** በፈቃድ አሰጣጥ እና ፈቃድ እድሳት ዙሪያ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ ለፍትህ፣ ለሲቪል ሰርቪስ ፣ለፖሊስ፣ለትምህርት ቢሮ እና ለሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎች እና ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷ ል፤ ** በዳግም ምዝገባ መምሪያ ላይ ለሁሉም የግል እና የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷ ል፤እና ** የዳግም ምዝገባ ሥራን ለሚያከናውኑ ባለሙያዎች የሥነ ምግባር እና ሙስናንን የመከላከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ #በዳግም_ምዝገባ_ስርዓት_የሰነድ_ምርመራ_የተደረገላቸው_ተቋማት_ካምፓሶች_እና_ፕሮግራሞች ** 290 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤533ካምፓሶቻቸው እና 3126ፕሮግራሞቻቸው፤ ** 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና 119 ካምፓሶቻቸው የሰነድ ምርመራ ሥራ ተጀምሯል፡፡ ** 84 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤254 ካምፓሶቻቸው እና 921 ፕሮግራሞቻቸው በዳግም ምዝገባ ሥርዓት ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ ** በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 75 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤116 ካምፓሶቻቸው እና 784 የዳግም ምዝገባ የሰነድ ምርመራ እና የመስክ ምልከታ ተደርጎላቸዋል፡፡ #ከከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት_የዳግም_ምዝገባ_ሥራ_የሚገኙ_ውጤቶች ** ተቋማት ተዛማጅ ካልሆኑ የንግድ መስኮች ጋር ተቀላቅለው እንዳይሰሩ ያደርጋል፤ ** ህጋዊ የአሰራር ስርዓት ተቋማት ላይ እንዲሰፍን ያደርጋል፤ ** ተቋማት በራሳቸዉ ህንጻ ወይም ሙሉ ህንጻ ተከራይተው ማስተማር እንዲችሉ ያደርጋል፤ ** ተቋማት ሰነዶቻቸውን በአዲሱ የጥራት መስፈርት መሰረት እንዲከልሱ ያደርጋቸዋል እና ** ተቋማት የመምህራን የትምህርት ዝግጅትና የቅጥር ሁኔታ በሚፈለገው ደረጃ እንዲያሟሉ ያስችላል፡፡ ** ተቋማት ለጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት ሰጥተዉ እንዲሰሩ ያበረታታል፤ ** ማህበረሰቡ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝ ያስችላል፤ ** ለህብረተሰቡአሁናዊ የትምህርት ጥራት መረጃ በመስጠት የጥራት ጠያቂ ማድረግ ያስችላል፤ ** ተቋማዊ መዋቅራቸዉን በመገምገም ውጤታማ የአስተዳደር ስርዓት እንዲኖራቸው እድል ይሰጣቸዋል፡፡ እና ** ተቋማት በተጨባጭ በጀት እንዲመሩ ያደርጋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።