ባለፉት አምስት ዓመታት የትምህርት እና ስልጠና ጥራትን በማረጋገጥ ሥራ የተገኙ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”

ባለፉት አምስት ዓመታት የትምህርት እና ስልጠና ጥራትን በማረጋገጥ ሥራ የተገኙ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” #የትምህርት_እና_ስልጠና_ጥራትን_በማረጋገጥ_ሥራ_የተገኙ_ኢኮኖሚያዊ_ስኬቶች፡- ** በግብርና፣በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ከፍያለ አስተዋጾ ማበርከት የሚችሉ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል፡፡ ** ይህም ለኢኮኖሚው መሻሻል አስተዋጾያመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ #የትምህርት_እና_ስልጠና_ጥራትን_በማረጋገጥ_ሥራ_የተገኙ_ማህበራዊ_ስኬቶች ** ሀገር በቀል እወቀቶች በስርዓተ ትምህርት እና በምርምር ስራዎች እንዲካተቱ፤ ** ትምህርት ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ሆኖ እንዳይታይ ለማድረግ፤ ** ውጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት እንዲዘረጋ እየሠራ መሆኑ ፤ ** የአካባቢያቸውን ባህልና የአኗኗር ዘዴ በውል ተገንዝበው ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሉ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል፡፡እና ** ሴቶችን፣የአካል ጉዳተኞችን እና ዝቅተኛ ገቢ ካለው የማህበረሰብ ክፍል የሚመጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተገቢው ሁኔታ ሳያቋርጡ እንዲያጠናቅቁ በማድረግ ፍትሀዊ የሆነ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል፡፡ #የትምህርት_እና_ስልጠና_ጥራትን_በማረጋገጥ_ሥራ_የተገኙ_ፖለቲካዊ_ስኬቶች ** በዕውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት ያደገ ማህበረሰብ ግንባታ፤ ** መልካም ስብዕና ያላቸው ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው፣ ራሳቸውን በአግባቡ መግለጽ እና መናገር የሚችሉ ፤ ** የአስተዳደር ክህሎትን የተካኑ ፣ ህግና ስርዓት የሚያከብሩ ፤እና ** የአካባቢያቸውን ባህልና የአኗኗር ዘዴ በውል ተገንዝበው ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሉ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል፡፡ #የትምህርት_እና_ስልጠና_ጥራትን_በማረጋገጥ_ሥራ_የተገኙ_ቴክኖሎጂያዊ_ስኬቶች ** ቴክኖሎጂ፣ምርምር እና ሀገር በቀል እውቀት እንዲስፋፋ፤ ** የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ሽግግር እንዲያድግ፤እና ** የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (Artificial Intelligence) በጥንቃቄ ለመጠቀም የሚያስችል ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::