ባለፉት አምስት ዓመታት የትምህርት እና ስልጠና ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ የተገኙ ስኬቶች! “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”
ባለፉት አምስት ዓመታት የትምህርት እና ስልጠና ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ የተገኙ ስኬቶች! “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” ** የትምህርት እና ስልጠና ጥራት መረጋገጥ የመንግስት ፣ የባለድርሻ አካላትና የማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት መወያያ አጀንዳ መሆኑ፤ ** መንግስት የትምህርት እና ስልጠና ጥራት መጓደል ችግር መፈታት ሀገር ልታሳካ ያሰበችውን የብጽግና ጉዞ ለማሳካት አንደኛው መፍትሄ እንደሆነ መረዳቱ፤ ** በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሙያ ማህበራት የሚገኙ ምሁራን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው፤ ** ሀገሪቱ ከፍተኛ ወጣት የሰው ሀይል ያላት በመሆኑ ይህንን ወጣት የኢኮኖሚ ዕድገቱ አቅጣጫና ገበያው በሚፈልገው ክህሎት ፣ እውቀትና ብቃት ካሰለጠኑት ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩ፤ ** በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ለመስጠት የሚያግዙ ያደጉና የዘመኑ የመረጃና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች እየተስፋፉ መምጣታቸው፤ ** ከኢንዱስትሪው ጋር በትብብር የመሥራት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ፤እና ** የፖለቲካ እና የልማት አጋሮች በጎ ፈቃድ እና ተነሳሽነት ተስፋ ሰጪ መሆን መቻሉ ናቸው፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
