በባለሥልጣኑ ለፕሮግራም እውቅና የወጣውን የጥራት ስታንዳርድ ላሟሉ በባለሥልጣኑ ተገምግሞ የሚሰጥ የጥራት ማረጋገጫ እውቅና አሰጣጥ ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”
በባለሥልጣኑ ለፕሮግራም እውቅና የወጣውን የጥራት ስታንዳርድ ላሟሉ በባለሥልጣኑ ተገምግሞ የሚሰጥ የጥራት ማረጋገጫ እውቅና አሰጣጥ ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች “የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!” #የተዘጋጀ_መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ #ስታንዳርዱ_የተዘጋጀባቸው_ባንዶች ** ህክምና እና ጤና ሳይንስ ** ግብርና ** ምህንድስና እና ኮምፒዩተር ሳይንስ ** ቢዝነስ እና ሂዩማኒቴስ እና ** የተፈጥሮ እና የቀመር ሳይንስ #ስልጠና_እና_የግንዛቤ_ማስጨበጫ ** በስታንዳርዶች እና በመገምገሚያ መሳሪያዎች ዙሪያ በአካል እና በበይነ መርብ (virtual) በመታገዝ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ባለሙያዎችን በመጋበዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የመስጠት ፤ እና ** የውጭ ገምጋሚ ባለሙያ ማሰልጠን #የተከናወኑ_ተግባራት ** ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ** የእውቅና አሰጣጥ ካውንስል ማቋቋም፤ ** የእውቅና አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ማድረግ፤ ** የፕሮግራም እውቅና ለጠየቁ ተቋማት የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎችን (Team of Assessors) በመላክ የዴስክ ሪቪው፣ ዶክመንት ስተዲና የመስክ ምልከታ ማድረግ፤እና ** የጥራት ስታንዳርዱን ለሟሉ ፕሮግራሞች እውቅና መስጠት፡፡ #በባለሥልጣኑ_ተገምግመው_እውቅና_ያገኙ_ፕሮግራሞች ** በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ18 ፕሮግራሞች ተገምግመውበእውቅና ካውንስሉ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ #እውቅና_ለተሰጣቸው_ተቋማትና_ፕሮግራሞች_የሚሰጡ_ማበረታቻዎች ** ተማሪን በልዩ ሁኔታ መመደብ፤ ** ለጥናትና ምርምር በልዩ ሁኔታ በጀት መመደብ፤ ** ለተቋሙ መምህራንና ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የትምህርት እድል መስጠት፤ ** ከባለስልጣኑ ጋር በመሆን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም እውቅና ያላቸውን ተቋማት ወይም ፕሮግራም ማስተዋወቅ፤ እና ** ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ወይም ባለድርሻ አካላት ጋር በልዩ ሁኔታ ትስስር እንዲፈጥሩ ድጋፍ ማድረግ፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
