ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ለሰኔ 2018ዓ.ም የመውጫ ፈተና ስለሚፈተኑ ተማሪዎች ብቁ እጩ ተፈታኞች የማጣርያ መስፈርቶች ይመለከታል፤ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ጠብቀው እንዲሰሩ የመከታተ
#ለሁሉም_የከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት #ባሉበት ጉዳዩ፦ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ለሰኔ 2018ዓ.ም የመውጫ ፈተና ስለሚፈተኑ ተማሪዎች ብቁ እጩ ተፈታኞች የማጣርያ መስፈርቶች ይመለከታል፤ ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ጠብቀው እንዲሰሩ የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚሁ መሰረት የሁሉም ከባለስልጣኑ ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ተማሪዎች ተመርቀው ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፍ ያለባቸው በመሆኑ ብቁ እጩ ተፈታኝ ሆኖ ለመቅረብ እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ኣለባቸው፦ 1. የተማሩበት ተቋም የተሰጠውን #ፈቃድ_ጊዜ_የትምህርት_መስክ_እና_ካምፓስ ማረጋገጥ፤ 2. በትምህርት ላይ ቆይታቸው #አራት_ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች #በመደበኛ_እና_ርቀት_መርሃ_ግብር በትምህርት መስኩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ #ለኤክስቴሸን_መርሃ_ግብር በትምህርት መስኩ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 3. የትምህርት ላይ ቆይታቸው #በአምስት_ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች #በመደበኛ_መርሃ_ግብር በትምህርት መስኩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ #ለኤክስቴሸን_መርሃ_ግብር በትምህርት መስኩ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 4. የትምህርት ላይ ቆይታቸው #ስድስት_ዓመት (ደ/ር ኦፍ ሜዲስን) ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች #በመደበኛ_መርሃ_ግብር በትምህርት መስኩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 5. የተፈታኝ ሙሉ ስም እስከ አያት መኖሩን ማረጋገጥ፤ 6. የተማሪዎች ወደ ተቋሙ በዝውውር የመጡ ካሉ የዝውውር ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ 7. ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀረቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በትምህርት መስኮችና በካምፓሶች የስነስርዓት ጥሰት የሌላቸው መሆኑ ማረጋገጥ፤ 8. ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሶፍትዌር ቴምፒሌቱ የሚያቀርቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በባለስልጣኑ የተመራቂ ተማሪዎች መረጃ ቋት በማስገባት የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ አገልግሎት የሚሰጥበት በመሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ትክክለኛና ታማኝ መረጃ በተሟላ ሁኔታ እንደያቀርቡ ከፍተኛ ሃላፊነት ያለባቸው መሆኑ አውቀው ይህ ሳይሆን ሲቀር ደግም ባለስልጣኑ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑ እናሳስባለን፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
