ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ በሰኔ 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃ ስለመጠየቅ ይመለከታል፤
#ለሁሉም_የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት #ባሉበት ጉዳዩ፦ በሰኔ 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃ ስለመጠየቅ ይመለከታል፤ ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------ የትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የመውጫ ፈተና በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ፈተናውን በዓመት ሁለት ጊዜ መሰጠት እንዳለበት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባሳወቀው መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከሚያዝያ 26/2018ዓ/ም እስከ ግንቦት 07/2018ዓ/ም ለማካሄድ የታቀደ በመሆኑ አስፈታኝ ለሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተጠቀሱ ቀናት ውስጥ ብቻ የተፈታኞች መረጃው በተለመደው ሲስተም እንዲያስገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉልን በማለት አሳውቋል፡፡ ስለሆነም በሰኔ 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ እጩ ተፈታኞች ለማጣራት ይቻል ዘንድ በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ካምፓስ በሰኔ 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከዚህ ደብዳቤ አባሪ በተደረገ ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከሚያዝያ 26/2018ዓ/ም እስከ ግንቦት 07/2018ዓ/ም ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንድታስገቡ እናሳስባለን፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
