በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/ 2016 መሠረት የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎች፡-

በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/ 2016 መሠረት የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎች፡- -------------------------------------------------------------------------- ** #መደበኛ_ትምህርት_ማለት በቀን ክፍለ ጊዜ የሚሰጥ ትምህርት ነው። ** #የበይነ_መረብ_መስመር_ትምህርት (Online learning) ማለት ሙሉ በሙሉ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን በመጠቀም በበይነ መረብ አማካኝነት ተማሪ በአካል መገኘት ሳያስፈልገው ባለበት ቦታ ሆኖ ትምህርቱን እንዲከታተል በማድረግ የሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ** #የርቀት_ትምህርት_ማለት ፈቃድ በተሰጠበት ከተማና አካባቢ እስከ 50 ኪ.ሜ ራዲየስ የሚሸፍን በቦታ የተገደበ ሆኖ ቢያንስ በአንድ ተርም ሁለት(2) ጊዜ ተማሪዎች በአካል እየተገኙ የገጽ ለገጽ ትምህርት የሚሰጥበት የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ** #ተከታታይ_ትምህርት_ማለት በማታ፡ በቅዳሜና እሁድ ወይም በክረምት ትምህርት የሚሰጥበት የመርሃ ግብር ነው። ** #የማታ_ትምህርት_ማለት በማታ ክፍለ ጊዜ ትምህርት የሚሰጥበት ዘዴ ሆኖ በዓመት እኩል የተከፋፈሉ ሶስት ሴሚስተሮች ክረምትን ጨምሮ የሚሰጥበት ዘዴ ነው። ** #የሳምንቱ_መጨረሻ_ትምህርት_ማለት በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜና እሁድ ክፍለ ጊዜ የሚሰጥ ሆኖ በዓመት እኩል የተከፋፈለ ሶስት ሴሚስተሮች ክረምትን ጨምሮ የሚሰጥበት ዘዴ ነው። ** #የክረምት_ትምህርት_ማለት በክረምት ወራት የሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ** #ድንበር_ተሻጋሪ_ማለት ውጭ ሀገር እውቅና ያለው ተቋም ሀገር ውስጥ ከሚገኝ ፈቃድ ወይም እውቅና ካለው ተቋም ጋር በመተባበር ወይም እውቅና ያለው የውጭ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሀገር ውስጥ ፈቃድ በማውጣት የሁለተኛ ዲግሪ እና ሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር በጋራ ወይም በተናጠል የሚሰጥበት የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ