ከትምህርት ሴክተር ለመውጣት የሚፈልጉት ተቋማት የሚከተሉትን የመውጫ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡-
ከትምህርት ሴክተር ለመውጣት የሚፈልጉት ተቋማት የሚከተሉትን የመውጫ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡- ------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ** ኦሪጅናል የፈቃድ ሰርቲፊኬት መመለስ፤ ** ፈቃድ ካለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ጋር የውል ስምምነት በማድረግ ፈቃድ በነበረው ወቅት የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው በተቋሙ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር እና የትምህርት ማስረጃ እንደሚከተለው ማስረከብ፤ ** ተማሪዎቹ ሲመዘገቡ በመግቢያነት ያስያዙት የትምህርት ማስረጃ፣ ** ተማሪዎቹ የመለሱት መታወቂያ ካርድ፣ ** የተማሪዎቹ ስም ዝርዝር፤ ** ተማሪዎቹ የተመረቁበት/የተማሩበት ፕሮግራም ስም፣ ደረጃ እና ሞዳሊቲ፤ ** ተማሪዎቹ በተቋሙ የተመዘገቡበት ዓመተ ምህረት፤ ** ተማሪዎቹ በተቋሙ ትምህርታቸውን የጨረሱበት ዓመተ ምህረት፤ . ** የተማሪዎቹ የመጨረሻ ሴሚስተር ኮሙሌቲቭ ውጤት፤ ** የሴኔት/አካዳሚክ ኮሚሽን የተመራቂ ተማሪዎች ቃለ-ጉባኤ፤ (ወቅቱን ጠብቆ የተዘጋጀ፤ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ የሚቀርብ) ** የተማሪዎችን ስም ዝርዝር እና የትምህርት ማስረጃ ያስረከበበትን ቀሪ የውል ስምምነት ሰነድ እና ቃለ ጉባኤ ማስገባት፤ ** ተቋሙ ከምንም ዓይነት የመንግስት እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ፤ ** የሚጠበቅበትን የስራ ግብር፣ የቤት ኪራይ፣ የስልክ፤ የመብራት፤ የውሀ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ከፍሎ ያጠናቀቀ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ፤ እና ** ከወንጀል ነጻ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
