በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/ 2016 መሠረት የተቋማት ደረጃ ስያሜን በተመለከተ ፡-

በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/ 2016 መሠረት የተቋማት ደረጃ ስያሜን በተመለከተ ፡- ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ** ተቋማት የደረጃ ስያሜ የሚሰጣቸው በሚቋቋሙበት ጊዜ ወይም የመጀመሪያ ፈቃድ በሚሰጣቸው ወቅት ወይም ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሥራ ላይ እያሉ የደረጃ ስያሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ እና መስፈርቱን ሲያሟሉ ሆኖ ቀጥሎ ባሉት የደረጃ ስያሜ መሠረት ይሆናል፤ #ኢንስቲትዩት_ደረጃ_ስያሜ_የሚሰጠው ** በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 13 መሠረት በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ በአንድ የትምህርት ዓይነት በዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት መስጠት የሚችል እና ባለሥልጣኑ የሚያወጣቸውን ዝርዝር መስፈቶች ሲያሟላ የሚሰጥ ስያሜ ነው ፤ ** የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ በደረጃ 1 እና 2 ላይ የሚመደቡ የሙያ መስኮችን በማካተት አጫጭር ስልጠናን ጨምሮ ትምህርትና ስልጠና ለሚሰጥ ተቋም የሚሰጥ ስያሜ ነው፤ #ኮሌጅ_ደረጃ_ስያሜ_የሚሰጠው **በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 13 መሠረት በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ ከዲፓርትመንት በላይ በሆነ አንድ የትምህርት ክፍል በዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት የሚሰጥ እና ባለስልጣኑ የሚያወጣቸውን ዝርዝር መስፈቶች ሲያሟላ የሚሰጥ ስያሜ ነው፤ ** የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ከደረጃ 1 እስከ 4 ላይ የሚመደቡ የሙያ መስኮችን በማካተት ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥ ተቋም ነው፤ #ዩኒቨርስቲ_ኮሌጅ_ደረጃ_ስያሜ_የሚሰጠው **በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በአዋጅ ቁጥር በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 11 መሠረት ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 3 የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ እንዲሁም ባለሥልጣኑ የሚያወጣቸውን ዝርዝር መስፈቶች ሲያሟላ የሚሰጥ ስያሜ ነው፤ ** ማንኛውም ተቋም ወይም ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን ካጓደለ፤የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ህጎችን ከጣሰ እና የእግድ ቅጣት ተላልፎበት ካላሻሻለ ባለሥልጣኑ የሰጠውን ፈቃዱ ይሰረዛል፤ #ፖሊ_ቴክኒክ_ኮሌጅ_ደረጃ_ስያሜ_የሚሰጠው ** በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ከደረጃ ከ1 እስከ 5 ላይ የሚመደቡ የሙያ መስኮችን በማካተት ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥ ተቋም ነው፤ #ዩኒቨርሲቲ_ደረጃ_ስያሜ_የሚሰጠው ** በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በአዋጅ ቁጥር በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 10 መሠረት ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 3 የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ እንዲሁም ባለሥልጣኑ የሚያወጣቸውን ዝርዝር መስፈርቶች ሲያሟላ የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ