በአገልግሎት አሰጣጥ እና በቅሬታ አፈታት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

በአገልግሎት አሰጣጥ እና በቅሬታ አፈታት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ------------------------------------------------------------------------- መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በቅሬታ አፈታት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በባለሥልጣኑ የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ደስታ ተክለአረጋይ የአገልግሎት አሰጣጥ ጽንሰ ሀሳብ አገልግሎት ማለት በአጠቃላይ የሰዎችን ማህበራዊ ፍላጐት ለማሟላት የሚካሄድ ማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ፤ከውጤት ጋር በተመጣጠነ ወጪ የሚሰጥ እና በተቋማት ውስጥ የሚካሄዱትን ተግባራት በሥርዓት ማደራጀትና መምራትን ወዘተ. የሚመለከት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ ደስታ የአገልግሎት አሰጣጥ ድክመቶች እና ችግሮች መካከል የሕዝብ አገልጋይነት አመለካከት እምብዛም አለመዳበር፤ የዜጎች አገልግሎት የማግኘት መብት ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፤ግዴታን ባለመወጣት ተጠያቂ አለመሆን፤ የተንዛዛና ኋላቀር አሠራርን መከተል፤አገልግሎት ለመስጠት የተገልጋዩ ፍላጐት ሳይሆን የመ/ቤቱ አስተዳዳራዊ አመቺነት ብቻ እንዲታይ ማድረግ፤በግብዓቶችናበቁጥጥር ላይ ብቻ ማተኮር፤ለተጠቃሚው ሕዝብ መረጃ መስጠት አለመቻል፣ ቢኖርም ውስንነት ያለበት መሆኑ እና ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ አለመኖር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ስለአገልግሎት አሰጣጥ፤ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ፅንሰ ሃሳብ፤ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ዋና ዓላማ፤ስለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የአገልግሎት አሰጣጥ ድክመቶችና ችግሮች ፤ ስለአገልግሎት አሰጣጥ አቅጣጫዎች፤ ለአገልግሎት ተጠቃሚነት ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ግልጽ ማድረግ፤ አገልግሎትበቀላሉ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት እና ቅሬታ የሚስተናገድበትን ሥርዓት መዘርጋት ቀርበው ማብራሪያና ገለጻ አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በአሰልጣኙ በአቶ ደስታ ተክለአረጋይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረኩ ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ