ከባለስልጣኑ የተላለፈባቸውን ውሳኔ ተግባራዊ ያላደረጉ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትን ሰለማሳወቅ የተላለፈ ማሳሰቢያ

#ለሁሉም_ብሄራዊ_ክልላዊ_መንግስት_ርዕሰ_መስተዳድር_ፅ_ቤቶች #ለአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_ከንቲባ_ፅ_ቤት #ለድሬዳዋ_ከተማ_አስተዳደር_ከንቲባ_ፅ_ቤት #ለሁሉም_ብሄራዊ_ክልላዊ_መንግስት_እና_ከተማ_አስተዳደር_ፍትህ_ቢሮዎች #ለሁሉም_ብሄራዊ_ክልላዊ_መንግስት_እና_ከተማ_አስተዳደር_ፖሊስ_ኮሚሽን_ፅ_ቤቶች_እና_ከተማ_አስተዳደር_ሲቪል_ሰርቪስ_ኮሚሽ_ፅ_ቤቶች #ለሁሉም_ብሄራዊ_ክልላዊ_መንግስት_እና_ከተማ_አስተዳደር_ንግድ_ቢሮዎች #ባሉበት #ጉዳዩ_ከባለስልጣኑ_የተላለፈባቸው_ውሳኔ_ተግባራዊ_ያላደረጉ_በከፍተ_ትምህርት_ዘር_የተሰማሩ_ተቋማት_ሰለማሳወቅ_፤ --------------------------------------------------------------------------------------------------------------- የኢ. ፌ. ዲ. ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር መሰረት በማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የባለስልጣን መ/ቤታችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ ስራ ክፍል በቀን 07/07/2018ዓ/ም በፃፈው ደብዳቤ የዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ባለመግባታቸው ምክንያት ከከፍተኛ ትምህርት ሴክተር እንዲወጡ የታዘዙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር አሳውቆናል፡፡ እንዲሁም ተቋማቱ አራት ጊዜ (ጥቅምት 15/2017ዓ/ም፣ ታህሳስ 02/2017ዓ/ም፣ ጥር 22/2017፣ ነሃሴ/2017ዓ/ም) በደብዳቤ፣ አንድ ጊዜ (ጥቅምት 2018 ዓ/ም) በስልክ እንዲሁም አንድ ጊዜ (ታህሳስ 20/2018) በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ በስልክ ጥሪ የቀረበላቸው መሆኑ በመግለፅ ለተቋማቱ በተደጋጋሚ ጥሪ የተደረገ ቢሆንም የሚጠበቅባቸውን መስፈርት እና ሂደት በማሟላት ከትምህርት ሴክተር ያልወጡ መሆኑ አሳውቆናል፡፡ ስለሆነም ተቋማቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንድያደርጉ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ህጋዊነታቸው የተቋረጠ ሰለሆነ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርተው ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እንድታደርጉልን እንዲሁም እስካሁን ያደረሱት ጉዳት ካለ በመፈተሽ በእናንተ በኩል አስፈላጊ የህግ እርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከወዲሁ እያሳሰብን የተቋማት ስም ዝርዝር 1 (አንድ) ገፅ አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የተቋማት ስም ------------- 1 አቢሲኒያ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ 2 አፍራን ቀሎ ኮሌጅ 3 አገው ምድር ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 4 አዲስ ፋና ኮሌጅ 5 ቢኤ ኮሌጅ 6 ኡቡንቱ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 7 ፈጣም ኮሌጅ 8 ግሪን የምርምርና የልማት ተቋም 9 ሴንቸሪ ኮሌጅ 10 ኮቻ ኪድማስ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 11 ካንድል ላይት የርቀት ትምህርት ኮሌጅ 12 ቀይ ባህር ኮሌጅ 13 ማራኪ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ 14 ኒው ዲፕሎማት ኮሌጅ 15 ፒቢቲ አፍሪካ ኮሌጅ 16 ኳሊቲ ስኮላር ኮሌጅ 17 ራዲካል ኢንተርናሽናል ኮሌጅ 18 ውቅያኖስ ኮሌጅ 19 የኔታ ኢንጅነሪንግ ኮሌ 20 ቪዥነሪስ የድህረ ምረቃ ኮሌጅ 21 ባቱ ግሎባል ኮሌጅ 22 ባህረ ጥበብ ጤናና ቢዝነስ ኮሌጅ 23 ማይክሮ ቢዝነስ ኮሌጅ 24 ማያ ኮሌጅ 25 ትሪፕል ኮሌጅ 26 ቤታሎጎ ኮሌጅ 27 ቤካ ኮሌጅ 28 ቀስተ ደመና ኮሌጅ 29 ብራይት ቪዥን ኮሌጅ 30 ኤ.አር.ቲ ሜዲካል ኮሌጅ 31 ኢሊያስ ኮሌጅ 32 ሳይፕሮ ኮሌጅ 33 ዳይናሚክ ኮሌጅ 34 ግራንድ ማርክ ኮሌጅ 35 ዱርማን ኮሌጅ 36 ህብረት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 37 አይቤክስ ሆቴልና ቱሪዝም ኮሌጅ 38 አይ ኪው ኮሌጅ 39 ገራይ ኮሌጅ 40 ጋላክሲ ቢዝነስና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ 41 ቪዥን ላንድ ኮሌጅ 42 መራ ሄመንገድ ኮሌጅ 43 ዩናይትድ ኦሮሚያ ኮሌጅ 44 ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኮሌጅ 45 ሲምለስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ 46 ዛክቦን ኮሌጅ 47 ኤም ኤስ ኤል ጂ ኮሊጅ 48 ስሪሳይ ኮሌጅ 49 ፋም ኮሌጅ 50 ስማርት ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 51 ሊድስታር ኮሌጅ ኦፍ ቢዝነስና ሊደርሺፕ 52 ዳሎል የቲክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ