በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት ስለተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ ቅድመ ሁኔታዎች
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
#የተቋም_እውቅና_ቅድመ_ሁኔታ
ማንኛውም ተቋም የተቋም እውቅና ሊጠይቅ የሚችለው የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ሲችል ብቻ ነው::
** ተቋሙ ከባለስልጣኑ በከፍተኛ የትምህርት የማስተማር ፈቃድ ያለው ወይም በከፍተኛ ትምህርት
ዘርፍ እንዲሰራ በፌደራል ወይም በክልል መንግስታት ስልጣን ባለው አካል የተቋቋመ ሊሆን ይገባል፤
** ተቋሙ ቢያንስ በአንድ ፕሮግራም አንድ ዙር ያስመረቀ መሆን ይገባዋል፤
** ተቋሙ የተቋም እውቅና ከመጠየቁ በፊት በባለስልጣኑ ተቋማዊ ጥራት ኦዲት ያካሄደ መሆን አለበት፤ እና
** ተቋሙ በባለስልጣኑ ለተቋም እውቅና አሰጣጥ ሥራ የተቀመጠውን የክፍያ መጠን መክፈል ይኖርበታል፡፡
#የፕሮግራም_እውቅና_ቅድ_መሁኔታ
ማንኛውም ተቋም የፕሮግራም እውቅና ሊጠይቅ የሚችለው የሚከተሉትን ማሟላት ሲችል ብቻ ነው::
** ተቋሙ ከባለስልጣኑ በፕሮግራሙ የማስተማር ፈቃድ ሊኖረው ይገባል፤
** ተቋሙ የፕሮግራም እውቅና ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው ፈቃድ ባገኘበት አግባብና ደረጃ መሆን ይገባዋል፤
** ተቋሙ በፕሮግራሙ ቢያንስ አንድ ዙር ተማሪዎችን ያስመረቀ መሆን ይገባዋል፤ እና
** ተቋሙ በባለስልጣኑ ለፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ ሥራ የተቀመጠውን የክፍያ መጠን መክፈል ይኖርበታል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት ስለተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ ቅድመ ሁኔታዎች
ETA
Education & Training Authority
January 16, 2026
1 min read