የእውቅና ካውንስል የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የፕሮግራም እውቅና ረቂቅ ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ
የእውቅና ካውንስል የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የፕሮግራም እውቅና ረቂቅ ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ --------------------------------------------------------------------------------- የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው አዜማን ኢንተርናሽናል ሆቴል የእውቅና ካውንስል የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የፕሮግራም እውቅና ረቂቅ ሪፖርት የግምገማ መድረክ አካሄደ። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የባለሥልጣኑ የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንካና ንጉሣ የእውቅና ስራ ከተጀመረ ከሶስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ እና ከዚህ ቀደም ከተካሄደው የፕሮግራም እውቅና ረቂቅ ሪፖርት የግምገማ የአሁኑ የተለየ እና ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን የሚያሳየው አውቶሚትድ መሆኑና ለእውቅና ሥራ ተብሎ የለማው ሶፍትዌር ለቀጣይ ሥራ ዝግጁ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡አንዳንድ ዪኒቨርሲቲዎች የውስጥ የእውቅና ካውንስል ማቋቋም መጀመራቸው የዘርፉ እድገት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ተሞክረው ወደ ሁሉም ተቋማት ሊስፋፋ የሚገባ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የተቋማት እውቅና ለማግኘት ጠንክረው መስራታቸው ሥራችንን ውጤታማ እና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ያስቻለው ቢሆንም ተቋማት በሚፈለገው ልክ በተለይም ትልቅ ውጤት ያመጣል ተብሎ በተዘጋጀው ስታንዳርድ መሠረት መዘጋጀት አለመቻላቸው አላስፈላጊ ምልልስ እና ተግዳሮት እየፈጠረ ነው ብለዋል፡፡ በመድረኩም የአርሲ ፣ የደብረብርሃን እና የአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲዎች የሚድዋይፈሪ ፕሮግራም ፤ የደብርብረሃን ዪኒቨርሲቲ የነርሲንግና የሚዲስን ፕሮግራም እንዲሁም የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋ ፣የደብረብርሃን እና የባህርዳር ዪኒቨርሲቲ የአኒስቲዢያ ፕሮግራም የሰነድ እና የመስክ ግምገማ ሪፖርት በባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ ባለሙያዎች በሆኑት በዶ/ር ግዛቸው ዮናስ፣ በወ/ሪት ፋሲካ ተመስገን፣በአቶ ባጫ ድሪባ፣በአቶ ሰለሞን በጋሻው፣በአቶ አቦነህ ተስፋዬ፣ በአቶ አብዱራህማን ያሲን እና በአቶ ታምሩ መስፍን ቀርቧል፡፡ የእውቅና አሰጣጥ ካውንስሉ የቀረቡትን የሰነድ እና የመስክ ግምገማ ሪፖርቶች ላይ በሰፊው ተወያይቶ እና በጥልቀት ገምግሞ በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች አቅጣጫ በማስቀመጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የፕሮግራም እውቅና ረቂቅ ሪፖርት የግምገማ መድረክ ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
