የባለስልጣኑ ሠራተኞች በተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀት ላይ ተወያዩ

የባለስልጣኑ ሠራተኞች በተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀት ላይ ተወያዩ -------------------------------------------------------------------------------------------- የባለሥልጣኑ ዓላማ ፈጻሚ እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ታህሳስ 17 ቀን 2018ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀት ላይ ተወያዩ፡፡ የተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና የባለሥልጣኑ አደረጃጀትን የተመለከተ የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የጥራት ኦዲት መሪ ሥራ አስፈጻሚና የሪፎርም ኮሚቴው ጸሀፊ ወ/ሮ ትዕግስት ኃይለስላሴ እንዳሉት ሪፎርሙ በፍቃድ አሰጣጥ፣ ቁጥጥር እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥላይ ከማተኮር ወጥቶ የጥራት ማህበረሰብ መፍጠር በሚያስችል መልኩ ለማደራጀት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው በሪፎርሙ አስፈላጊነት፤ አሁን ያለው የባለስልጣኑ የመፈጸም ብቃትና መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ በአሁናዊ ተግዳሮቶች እና ወደ ሪፎርም ከተገባ በኋላ በሚኖሩ ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ እና ገለጻ አድርገዋል፡፡ የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ የጥራት ኦዲት መሪ ሥራ አስፈጻሚ መሪ ሥራ አስፈጻሚና የሪፎርም ኮሚቴው ጸሀፊ ወ/ሮ ትዕግስት ኃይለስላሴ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::