በተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀት ላይ ውይይት ተደረገ

በተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀት ላይ ውይይት ተደረገ --------------------------------------------------------------------------------------- የባለሥልጣኑ መካከለኛ አመራሮች ታህሳስ 15 ቀን 2018ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀት ላይ ተወያዩ፡፡ የተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም እና በባለሥልጣኑ አደረጃጀትን የተመለከተ የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን እና ብቃት ማእቀፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚና የሪፎርም ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ሀብታሙ ተሾመ እንዳሉት የሪፎርም ሥራ ላይ በየደረጃው ግልጽነት የመፍጠር ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው በሪፎርሙ አስፈላጊነት፤ አሁን ያለው የባለስልጣኑ የመፈጸም ብቃትና መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ በአሁናዊ ተግዳሮቶች እና ወደ ሪፎርም ከተገባ በኋላ በሚኖሩ ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ምከረ ሀሳቦችን ከተቋሙ ተግባርና ሀላፊነት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመነሳት ሰፊ ማብራሪያ እና ገለጻ አድርገዋል፡፡ በቀጣይ የባለስልጣኑ አደረጃጀት ከቁጥጥር ባለፈ የትምህርት ጥራት ባህል በመፍጠር የጥራት ማህበረሰብ መገንባትን መሠረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን እና ብቃት ማእቀፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚና የሪፎርም ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ሀብታሙ ተሾመ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::