ባለስልጣኑ ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እየተጠቀመበት ካለው ሲስተም (System) ወይም የሶፍትዌር አፕልኬሽን ከሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸው እና ተመራቂዎቻቸው ከያዘ ሲስተም ጋር ትስስር (System Integration) ማድረግን በተመለከተ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ጀምሮ በበየነ መረብ ስብሰባ ይደረጋል፡፡

ለክቡራንና ክቡራት! የኢ.ፌ.ድ.ሪ ትምህርት ስልጠና ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና በደንብ ቁጥር 515/2015 በመቋቋም የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፤ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ ከሀገር ውስጥ የትምህርት ተቋማት የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እና ከሀገር ውጭ የተገኘ የትምህርት ማስረጃን አቻ ግምት መስጠት ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማረጋገጥ የመጀመሪያው መስፈርት የተመራቂዎች መረጃ ከተማሩበት ተቋም ተምረው የተመረቁ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ነው።ስለሆነም ይህንን መረጃ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማግኘት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እየተጠቀመበት ካለው ሲስተም (System) ወይም የሶፍትዌር አፕልኬሽን ከሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸው እና ተመራቂዎቻቸው ከያዘ ሲስተም ጋር ትስስር (System Integration) በመሥራት ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም የስራውን አስፈላጊነት እና ከተቋማችሁ ሲስተም ጋር ለሚሰራው የትስስር (integration) ስራ ገለጻ እና ውይይት ለማድረግ ፕሮግራም ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ጀምሮ በበየነ መረብ ስብሰባ ለማድረግ እቅድ ተይዟል። ስለሆነም በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚመለከተውን የበላይ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በዚህ ሊንክ በመግባት እንድትሳተፉ እሳሳባለን። https://us05web.zoom.us/j/88221199205... ማሳሰቢያ፣ ለሚኖራችሁ ጥያቄ በስልክ ቁጥር 0922023232 ወይም 0911876072 መጠየቅ ትችላላችሁ።