በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የህንፃ ለውጥ ያደረገ ተቋምን በተመለከተ፡-

በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የህንፃ ለውጥ ያደረገ ተቋምን በተመለከተ፡- ** ማንኛውም ተቋም ከባለስልጣኑ ከተፈቀደለት ፈቃድ ውጭ የህንፃ ለውጥ ማድረግ አይችልም፤ ** ተቋሙ ያለ ባለስልጣኑ ፈቃድ የህንፃ ለውጥ ባደረገበት ካምፓስ ወይም ቅርንጫፍ ማዕከል ላይ ለ2 ዓመት ትምህርት እንዳይሰጥ ቅጣት ይጣልበታል፤ ** ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አግባብ የህንፃ ለውጥ ባደረገበት የተሰጠ የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፤ እና ** ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም፣ ካምፓስ ወይም ቅርንጫፍ ማዕከል እንዲዘጋ ይደረጋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።