የባለሥልጣን መ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጋራ አከበሩ

ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራርና ሠራተኞች የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት መከበር ሕገ መንግሥታዊ ዋስትናን ያረጋገጠውን የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የጸደቀበትንና ለ20ኛ ጊዜ "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን በዓል በዛሬው ዕለት በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በጋራ አክብረዋል፡፡ ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ልዩ የሚያደርገው በተለይም የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ተጠነናቆ የተመረቀበት፤ ኢትዮጵያ ማንሰራራት የጀመረችበትና ከፍተኛ የሆኑ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እውን የሆኑበት ጊዜ ላይ የምንገኝ በመሆኑ እንደሆነ በመድረኩ መክፈቻ ወቅት የተወሳ ሲሆን፤ ከዚህ አንጻር በትምህርት ዘርፉ ላይ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ በቀጣይ የተሻሉ ተግባራትን ለማከናወን ይህ በዓል እንደ መነሻ መሰውድ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግሩ ያደረጉት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ መስፍን በዴሞክራሲ እና በፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ያሉትን ተስፋዎችና የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች እንዲሁም በሀገራዊ ሪፎርሙ፣ በተሰሩ የልማት ስራዎች እና በመሰል ተግባራት የተጓዝንባቸውን ርቀቶች በማስታወስ የእርቀ ሠላም ኮሚሽን በሀገራችን ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የጀመራቸውን ጥረቶች ከዳር ለማድረስ የሁሉንም ዜጋ ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ”ዴሞክራሲ እና የፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፡ ተስፋዎቹና ተግዳሮቶቹ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ በባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ የቀረበ ሲሆን፤ በዚህም የዴሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና የሕግ የበላይነት፤ ምርጫ እና ሰብዓዊ መብት፣ የውክልና ሥልጣን ባለቤትነት ተግባራዊ ስለሚደረግበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ የፌዴራል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተስፋዎች መካከል ለክልሎች ሙሉ በሙሉ ነጻ፤ እውነተኛና ምቹ የሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር ስርዓት መገንባቱ፣ ማሕበራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራዎች መጠናከር እንዲሁም የተጀመሩ የተቋማት ግንባታ ሥራዎችና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ስራዎች የኢትዮጵያ ቀጣይ ተስፋዎች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ሀሳብና አስተያየቶች ከመድረክ ምላሽ በመስጠት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።