በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የተማሪ መረጃ አያያዝ፡ አጠባብቅና አላላክን በተመለከተ፡-
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የተማሪ መረጃ አያያዝ፡ አጠባብቅና አላላክን በተመለከተ፡- ** ማንኛውም ተቋም የተማሪዎችን መረጃ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በተሟላ መልኩ በአግባቡ መያዝና መጠበቅ እና ለሚመለከተው አካል በተቀመጠው እና በተጠየቀበት ወቅት በሚያዘጋጀው ቅጽ መላክ አለበት፤ ** በትምህርት አመቱ የመዘገባቸውን አዲስ ተማሪዎች ዝርዝር መረጃ ትምህርት በተጀመረ በ2 ወር፣ የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዝር የምርቃት ጊዜው ባበቃ በ45 ቀናት ውስጥ ለባለስልጣኑ ማስገባት አለበት፤ በቅበላ ወቅት ካቀረበውተማሪዎች ቁጥር እና ዝርዝር ውጪ ተመራቂ ተማሪዎችን ማቅረብ አይችልም፤ ተቋሙ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አለማደራጀቱ እና በወቅቱ አለማቅረቡ ሲረጋገጥ፡- ** ተገቢውን መረጃ አደራጅቶ ለባለስልጣኑ በ20 ቀናት ውስጥ እንዲያቀርብ እንዲሁም የመጨረሻ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው ይደረጋል፤ ** ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ካልተፈጸመ ተቋሙ ወይም ካምፓሱ ወይም ማዕከሉ አስፈላጊውን መረጃ ባላደራጀበት እና ባላቀረበበት የትምህርት መስክ ለ 2 ዓመት የሚቆይ አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይልበታል፤ እና ** ከላይ በተጠቀሰውን ቅጣት ሊታረም ያልቻለ ተቋም ወይም ካምፓሱ ወይም ማዕከሉ ወይም የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።
