ስለእውቅና አሰጣጥ ምንነት፤ ህጋዊ መሠረት፤ ስለ እውቅና ዓይነቶች፤የተቋማዊ እውቅና እና የፕሮግራም እውቅና ለመጠየቅ መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች
ስለእውቅና አሰጣጥ ምንነት፤ ህጋዊ መሠረት፤ ስለ እውቅና ዓይነቶች፤የተቋማዊ እውቅና እና የፕሮግራም እውቅና ለመጠየቅ መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች ----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሚኒስትሮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1263/2014 የተቋቋመ ሲሆን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣንን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 515/2014 እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የተቋምና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 989/2016 መሠረት በፌደራል መንግሥት አካላት ለተቋቋሙ፣ በፌደራል ደረጃ በግል ለተቋቋሙ፤ በውጪ ዜጐች ለተቋቋሙ፣ በሌላ ሀገር ሕግ ለተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስር በሚተዳደሩ እንዲሁም በክልል አግባብነት ባላቸው አካላት ፈቃድ በተሰጣቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ባለሥልጣኑ ያወጣውን የጥራት ስታንዳርድ ስለማሟላታቸው ተገምግመው የስልጠና ጥራት ማረጋገጫ እዉቅና እንዲሰጥ ስልጣን ተሰጥቶታል። #የእውቅናዓይነቶች ** የተቋማዊ እውቅና እና ** የፕሮግራም እውቅና ናቸው፡፡ #ማንኛውም_ማሰልጠኛ_ተቋም_የተቋማዊ_እውቅና_ሊጠይቅ_የሚችለው_የሚከተሉትን_ሁኔታዎች_ማሟላት_ሲችል_ነው_። 1. ማሰልጠኛ ተቋሙ ከባለሥልጣኑ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የማሰልጠን ፈቃድ ያለው ወይም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ እንዲሰራ በፌደራል ወይም በክልል መንግስታት ስልጣን ባለው አካል የተቋቋመ ሊሆን ይገባል ፤(should be licensed by an authorized body) 2. ማሰልጠኛ ተቋሙ ቢያንስ በአንድ የስልጠና መስክ ለአንድ ዙር ያስመረቀ መሆን ይገባዋል፤እና 3. እውቅና ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው በካምፓስ ደረጃ ይሆናል። #ማንኛውም_የስልጠና_ተቋም_የፕሮግራም_እውቅና_ሊጠይቅ_የሚችለው_የሚከተሉትን_ሁኔታዎች_ማሟላት_ሲችል_ነው_። 1. በፌደራል ወይም በክልል አግባብነት ባላቸው አካላት በስልጠና መስኩ የማሰልጠን ፈቃድ ሊኖረው ይገባል፤ (should be licensed by an authorized body) 2. ማሰልጠኛ ተቋሙ በፕሮግራሙ ቢያንስ አንድ ዙር ሰልጣኞችን አሰልጥኖ ያስመረቀ መሆን ይገባዋል፤( must have graduated at least one batch of trainees in the program) 3. ማሰልጠኛ ተቋሙ የፕሮግራም እውቅና መጠየቅ የሚችለው ፈቃድ ባገኘበት የስልጠና ሙያና ደረጃ መሆን ይኖርበታል ፤(Training Profession and Level for which it is Licensed) 4. ማሰልጠኛ ተቋሙ የፕሮግራም እውቅና ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው በካምፓስ ደረጃ ይሆናል ፤(Campus Level) 5. ተቋሙ የተሟላ ማመልከቻ በAIMS (Accreditation Information Management System/ https://accreditation.neta.gov.et) አማካኝነት አስፈላጊ የሆኑ አጋዥ ሰነዶችን ማለትም የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ/ Data Collection Tool (DCT)፣ የሰልጣኞች እርካታ ዳሰሳ/ Trainees Satisfaction Survey (TSS) እና ግለ ግምገማ ሪፖርት/ Self-evaluation Report (SER), በማካተት ማቅረብ አለበት፤እና 6. የእውቅና ማመልከቻ በተቋሙ (TVETI) ፕሬዝዳንት/ዲን/ኃላፊ ተፈርሞ መቅረብ ይኖርበታል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
