ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ 2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃን ይመለከታል፤

ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ 2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃን ይመለከታል፤ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ጥራት ያለው ወቅታዊና የተሟላ መረጃ ሰብስቦ በመተንተን የቁልፍ አፈጻጸም አመላካቾችን (KPI) በየጊዜው ለመከታተል፣ እንዲሁም በዘርፉ ያለውን የመረጃ አቅርቦትና ጥራት ችግር በዘላቂነት በመፍታት የሚተላለፉ ውሳኔዎች፣ የሚቀረጹ የፖሊሲና ስትራቴጂ አቅጣጫዎች እና የእቅድና ግቦች ተአማኒነት ባለው መረጃ ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ እየተሰራበት ይገኛል። በዚሁ መሠረት የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት (Higher Education Management Information System) ተዘርግቶ ተቋማትም መረጃቸውን በሲስተም እንዲያስገቡ አካውንት በመፍጠር የአጠቃቀም ስልጠናዎች መስጠታችን ይታወሳል። በትምህርት ሚኒስቴር እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር በነበረው ውይይት በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ሁሉም ተቋማት መረጃቸውን በተዘጋጀው ሲስተም ላይ የማስገባት ግዴታ አለባቸው። መረጃውን የማያስገቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፌደራል መንግስት በሚሰጡ አገልግሎቶች እንደማይስተናገዱ አቅጣጫ ተቀምጧል። ስለሆነም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ሁሉም መረጃዎች ተሟልተውና በየተቋሙ አመራር ተረጋግጠው እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሲስተሙ በ`http://hemis.ethernet.edu.et` እንድታስገቡ እየጠየቅን ይህንንም ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ለኢፌድሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ኃላፊነት መሰጠቱን አሳውቃለሁ።