በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት ባለስልጣኑ የሰጠውን የፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልፅና ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ ያልለጠፈ ወይም ያላሳወቀ ተቋም

በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት ባለስልጣኑ የሰጠውን የፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልፅና ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ ያልለጠፈ ወይም ያላሳወቀ ተቋም ** ማንኛውም ተቋም በባለስልጣኑ የተሰጠውን ፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልፅና ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ መለጠፍ ወይም ማሳወቅ ይኖርበታል፤ ** ተቋሙ ተገቢውን ማስተካከያ በማድረግ በ 20 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያቀርብና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው ይደረጋል፤ ** ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ማስተካከያ ያላደረገ ተቋም ወይም ካምፓስ ወይም ቅርንጫፍ ማዕከል ለ 2 ዓመት አዲስ የተማሪ ቅበላ እንዳያደርግ ቅጣት ይጣልበታል፤ እና ** ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ማስተካከያ ያላደረገ ተቋም ወይም ካምፓስ ወይም ቅርንጫፍ ማዕከል እንዲዘጋ ይደረጋል ፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።