በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለስልጣኑ ተገምግሞ ተቀባይነት ያገኘውን ስርዓተ- ትምህርትን ሳይከተል ትምህርት የሰጠ ተቋም
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለስልጣኑ ተገምግሞ ተቀባይነት ያገኘውን ስርዓተ- ትምህርትን ሳይከተል ትምህርት የሰጠ ተቋም ** ማንኛውም ተቋም የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ ወይንም አቅጣጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት ተማሪ መቀበል፣ ማስተማርና ማስመረቅ አለበት፤ ** የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ ወይንም አቅጣጫ ሳይከተል በተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት ያስተማረ እና ያስመረቀ ተቋም በትምህርት መስኩ ለ2 ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል፤ እና ** ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም ስርዓተ-ትምህርቱን ያልተከተለ የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
