በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም ** ማንኛውም ተቋም ስልጣን ባለው አካል የወጣ የቅበላ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር አይችልም፤ ** ተቋሙ ከተቀመጠው የቅበላ መስፈርት ውጪ ምዝገባ ባካሄደባቸው የትምህርት መስኮች ለ 2 ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል ፤ ** ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም የቅበላ መስፈርት ያላሟላ የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል፤ ** የቅበላ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ያሰናብታል፤ በ 1 ወር ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት ያደርጋል፤ እና ** በዚህ መልክ የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በማንኛውም መልኩ ተቀባይነት አይኖራቸውም :: የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
