የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት የተቋም እውቅና እድሳት እና የፕሮግራም እውቅና እድሳት ማለት ፡-
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት የተቋም እውቅና እድሳት እና የፕሮግራም እውቅና እድሳት ማለት ፡- የተቋም እውቅና እድሳት ** በከፍተኛ ትምህርት መስክ ዕውቅና አግኝቶ ሲሰራ የቆየ ተቋም በባለስልጣኑ ዕውቅና እድሳት ለተቋም ዕውቅና እድሳት የወጣውን የጥራት ስታንዳርድ ስለማሟላቱ ባለስልጣኑ ወይም ባለስልጣኑ በወከለው አካል ተገምግሞ ለተቋም የሚሰጥ የጥራት ማረጋገጫ ነው፡፡ የፕሮግራም እውቅና እድሳት ** በከፍተኛ ትምህርት መስክ ዕውቅና አግኝቶ ሲሰራ የቆየ ፕሮግራም በባለስልጣኑ ለፕሮግራም ዕውቅና እድሳት የወጣውን የጥራት ስታንዳርድ ስለማሟላቱ ወይም ባለስልጣኑ በወከለው አካል ተገምግሞ ለፕሮግራም የሚሰጥ የጥራት ማረጋገጫ ነው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::
