‘የውስጥ ጥራትን ማረጋገጥ፤ ለቀጣይ መሻሻል እና ተአማኒነት ’ በሚል ርዕስ ሴሚናር ተካሄደ
‘የውስጥ ጥራትን ማረጋገጥ፤ ለቀጣይ መሻሻል እና ታማኝነት ’ በሚል ርዕስ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ሴሚናር ላይ የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የትምህርትና ስልጠና የውስጥ ጥራትና ክትትል መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ የውስጥ ጥራት የማረጋገጥ ሥራ ፖሊሲዎቻችን፣ አሰራራችንን እና ተግባሮቻችን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ከተልዕኮ፣ ከሀገር አቀፍ እና ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች እና ከባለድርሻ አካላት ፍላጎቶች የሚጠበቁ ለውጦች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ለሚያረጋግጥ ፤ለጥራት አረጋጋጭ ተቋማት ውጤታማነቸውን እና ተአማኒነታቸውን ለማረጋገጥ እና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ቦታዎችን በመለየት የግብረመልስ ዘዴዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውስጣዊ የአሰራር ስርዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ ዝናቡ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳብ ላይ ከተዳሰሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የውስጥ የጥራት ማረጋገጫ የውስጥ ጥራት ኦዲት ልዩነት እና አንድነት፤የውስጥ ጥራት ኦዲትን የማጠናከር አስፈላጊነት፤የውስጥ ማረጋገጫ ስታንዳርዶች፤የሌሎች ሀገራትና ተቋማት ተሞክሮዎች ፤ተግዳሮቶችና የሚፈቱበት ቀጣይ አቅጣጫዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ውይይቱን የመሩት በባለስልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ ዲስክ ኃላፊ አቶ ግዛቸው እሸቱ እና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ እና የሠራተኞች የሥራ አካባቢ ደህንነት ባለሙያ አቶ አባዲ አብረሃ የውስጥ ጥራትን የማረጋገጥ ስራ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከትምህርትና ስልጠና የውስጥ ጥራትና ክትትል ሥራ አስፈጻሚ የሥራ ክፍል ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች እና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተድርጎባቸዋል። በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽንና የብቃት ማረጋገጫ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀብታሙ ተሾመ ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልእክት ሴሚናሩ ጥሩ የእርስ በርስ መማሪያ መድረክ እንደነበረ አንስተው የውስጥ ጥራትን የማረጋገጥ ሂደት ቀጣይነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል ፡፡ በመጨረሻም አዘጋጁን የሥራ ክፍል፣ የመወያያ ሀሳብ አቅራቢውን እና የውይይቱን ተሳታፊዎች አመስግነዋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
