ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያ በቅድመ-ምረቃ እና በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር ተመዝጋቢዎች የሚከተሉትን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡- የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች በከፍተኛ ትምህርት በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ለመመዝገብ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይንም በቀድሞ 10+3 ወይንም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ለ2ኛ ዲግሪ ተመዝጋቢዎች በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡ ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያ መስፈርት የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡ ** ከተጠቀሱ መመሪያዎች ውጪ ገብተው ለሚማሩ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ መሆኑን እናሳስባለን። የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
