ባለስልጣኑ የሚያከናውነው የጥራት ኦዲት የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት

ባለስልጣኑ የሚያከናውነው የጥራት ኦዲት የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት:- 1) የጥራት ኦዲት ዋንኛ ዓላማ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቀጣይነት ያለው የትምህርት ጥራት መሻሻልን ለማረጋገጥ ያለመ ሲሆን የተቋማት ጠንካራ ጎኖችን እና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች በመለየት የመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ራዕይና ተልዕኮቻቸውን ማሳካት የሚያስችል ቀጣይነት ያለውና በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ የውስጥ ጥራት አጠባበቅ ስርዓት መተግበራቸውን ማረጋገጥ ነው። 2) የጥራት ኦዲት የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ውጤታማ የሀብት አጠቃቀምን በማረጋገጥ ተልዕኳቸውን መፈፀማቸውን በመገምገም ለባለድርሻ አካላት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ነው። 3) የጥራት ኦዲት በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ላይ ባለስልጣኑ ያከናወነውን የጥራት ኦዲት ግኝቶችን እና የተቋማቱን የውስጥ ጥራት አጠባበቅ ስርዓት የውጤታማነት ደረጃን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ባለድርሻ አካላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማድረግ እንዲችሉ፣ በትምህርት ስርዓቱ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ለማስቻል እና ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ ነው። 4) የጥራት ኦዲት ግኝቶችን ተከትሎ የተሰጡ ምክረ ሀሳቦችን በመጠቀም የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ፖሊሲዎቻቸውን፣ ስርዓተ-ትምህርቶቻቸውን እና የውስጥ ጥራት አጠባበቅ ስርዓቶቻቸውን ከሀገራዊ እና ተቋማዊ ተልእኮዎች ጋር አጣጥመው እንዲሰሩ ማድረግ ነው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።