የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 የተቋማት መብት እና ግዴታዎች
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 የተቋማት መብት እና ግዴታዎች ፡- የተቋማት መብት ** ተቋማት ስለ እውቅና አሰጣጥ ሂደት፣ ስለግለ-ግምገማ ዝግጅትና ስለትምህርት ጥራት አጠባበቅ በአጠቃላይ ከባለስልጣኑ ስልጠና ሲያስፈልጋቸው የስልጠና ድጋፍ ጠይቀው ማግኘት ይችላሉ፤ ** ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ማመልከቻ ካቀረበ በኋላ የእውቅና ግምገማ ጊዜ መርሀ ግብሩን የማወቅ መብት አለው እና ** እውቅና የተከለከለ ተቋም በቅሬታ አፈታት መምሪያ መሠረት ቅሬታውን ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይችላል፡፡ የተቋማት ግዴታ ** ተቋሙ ለገምጋሚ ባለሙያዎች ቡድን መረጃ እና ማስረጃ ማቅረብ እና የቡድኑ አባላት ለሚያነሷቸው ተያያዥ ጥያቄዎች መልስ መስጠትይኖርበታል እና ** ተቋሙ ግምገማው በሚከናወንባቸው ቀናት ውስጥ ገምጋሚ ቡድኑ ለሚያደርጓቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
