በኤች .አይ.ቪ /ኤድስ እና በሂፒታይተስ ቢ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ የሥራ ክፍል አዘጋጅነት በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በኤች .አይ.ቪ / ኤድስ እና በሂፒታይተስ ቢ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ በባለሥልጣኑ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ እና የሠራተኞች የሥራ አካባቢ ደህንነት ባለሙያ አቶ አባዲ አብረሃ ስለኤች .አይ.ቪ / ኤድስ እና ስለሂፒታይተስ ቢ ቫይረስ ምንነት፤መተላለፊያ እና የመካለከያ መንገዶች ፤የቫይረሱ ስርጭት የሚገኝበት ደረጃ እና በባለሥልጣን ደረጃ ከቫይረሶቹ ስርጭት እና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ዙሪያ ሰፋ ያላ ማብራሪያ እና ገለፃ አድርገዋል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ