ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡ የ2018 ዓ.ም የHEMIS መረጃን ይመለከታል ፤
ለትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ኃላፊነቶች አንዱ ሀገራዊ የትምህርት መረጃዎችን በማሰባሰብ የትምህርት ተደራሽነት፣አግባብነት፣ ጥራት እና ፍትሀዊነትን በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ማረጋገጥ ነው። በዚሁ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የቁልፍ አመለካቾች አፈጻጸም ለመከታተል የተሟላ እና ጥራት ያለው መረጃ በሚፈለገው ጊዜ በኦንላይን ማግኘት እንዲቻል ዘመናዊ የከፍተኛ ትምህርት መረጃ ስርዓት /HEMIS/ ዘርግቶ ትግበራ ላይ ውሏል። በዚህም ሂደት ውስጥ ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ጥቂት መንግስታዊ ያልሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰረታዊ የሚባሉ መረጃዎችን አስገብተዋል። ነገር ግን የተሰበሰበው መረጃ ለፖሊሲ ቀረጻ እና ለቁልፍ አመልካቾች ክትትል ለማድረግ ሙሉ መረጃ ከማግኘትት አንጻር በአንድአንድ ተቋማት ክፍተቶች ታይተዋል። በመሆኑም ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ በHEMIS የሚጠየቁ መረጃዎች ወቅታቸውን ጠብቀው በየጊዜው ሙሉ በሙሉ እንዲሞሉ እና በበላይ አመራሩ የመረጃው ጥራትና ተዓማኒነት ተረጋግጦ በhttp://hemis.ethernet.edu.et በተሰጣችሁ አካውንት እንዲላኩ እያሳሰብኩ፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የተሟላ መረጃ ወቅቱን ጠብቆ በማይልክ ተቋም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን በጥብቅ አሳውቃለሁ።