በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተከለከሉ እና የእርምት እርምጃ የሚያስከትሉ ተግባራት
** ፈቃድ ባልተገኘበት ተቋም ስልጠና መስጠት፤ ** ባልተፈቀደለት የሥልጠና መስክ ስልጠና እየሰጠ የተገኘ ተቋም፤ **ፈቃድ ሳያድስ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም፤ ** በባለሥልጣኑ ከተሰጠው የደረጃ ስያሜ ውጪ ሌላ የደረጃ ስያሜ ሲጠቀም የተገኘ ተቋም፤ ** በሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ከሚያዘጋጀው የሙያ ደረጃ እና ስርዓት ትምህርቱ ወጭ ሲያሰለጥን የተገኘ ተቋም፤ ** የሥልጠና መስክ አሰልጣኞች አዛውሮ ወይም ቀይሮ ሲገኝ፤ ** ስልጣን ባለው አካል የወጡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ስልጠና የሰጠ ተቋም፤ ** ከተፈቀደለት ሰልጣኝ ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያሰለጥን የተገኘ ተቋም፤ ** የተማሪ መረጃ አያያዝ፣ አጠባበቅና አላላክ፤ ** ባለሥልጣኑ የተሰጠውን የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልጽ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ ያለጠፈ ወይም ያላሳወቀ ተቋም፤ ** ባለሥልጣኑ የተሰጠውን የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልጽ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ ያለጠፈ ወይም ያላሳወቀ ተቋም እና ** ሐሰተኛ ሰነዶች እና ትክክለኛ አድርጎ ማቅረብ ናቸው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ - https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም - https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www.neta.gov.et ይከታተሉን፡፡