18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በባለሥልጣኑ ተከበረ
በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!”በሚል መሪ ቃል 18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ ፡፡ ዕለቱን የተመለከቱ መልእክቶችን በማስተላለፍ፤ በሉዓላዊነት መገለጫና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ምልክት በሆነው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ-መሀላ በመፈጸም እና ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር በዓሉ ተከብሮ ውሏል፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ